ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዱል ሳቡር ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሳቡር ከኸዝብ-ኢ ኢዝላሚ ጉልቡዲን (ኤችአይጂ) ጋር ትብብር ያለው የፈንጂዎች ባለሙያ ነው፡፡ በግንቦት 08 ቀን 2005 ዓ.ም. በካቡል፣ አፍጋኒስታን ላይ ተመሳስሎ በተሰራ ፈንጂ (ኢምፕሮቫይዝድ ኤክስክሎሲቭ ዲቫይስ) በተሽከርካሪ በማድረግ ለተፈፀመው ጥቃት ሀላፊነት የሚፈለግ ነው፡፡ በዚህ ጥቃት ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና አራት የዩናይትድ ስቴትስ ኮንትራክተሮች ተገድለዋል፡፡ ይህ ፍንዳታ ስምንት የአፍጋኒስታን ዜጎችን (ሁለት ህፃናትን አካትቶ) የገደለ ሲሆን፣ ሰላሳ ሰባት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ አድርሷል፤ የዩናይትድ ስቴትስ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ላይ ውድመት ደርሷል፡፡
ሳቡር እና የኤችአይጂ ፈንጂዎች ባለሙያ የሆነው አብዱላ ናውባሃር በአፍጋኒስታን ካቡር አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የውጭ ዜግነት ያላቸውን ሰራተኞች በማጓጓዝ ላይ በነበረ አውቶቡስ ላይ በመስከረም 08 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፈጸመው ተመሳሳይ የፈንጂ ጥቃት ከተሳተፉ ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ፍንዳታ 12 ሰዎችን ገድሏል፡፡
በመጋቢት 01 ቀን 2008 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳቡርን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሳቡር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልማግሪቢ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡
