አብደራዉፍ ቤን ሃቢብ ጅደይ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ | ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብደራዉፍ ቤን ሀቢብ ጅደይ፣ በሌላው ስሙ ፋሩቅ አል-ቱኒዚ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ጅደይ ከአል-ቃዒዳ (ኤኪው) አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት አለው ተብሏል፤ እንዲሁም አውሮፕላኖችን በመጥለፍ እና በሌሎች የሽብር ተግባሮች እቅድ ውስጥ ተሳትፎ ነበር፡፡ ጅደይ ተጠርጣሪ ሽብርተኛ ከሆኑት ፋከር ቤን አብደልአዚዝ ቦውሶራ (ሀይፐርሊንክ) ጋር ተባባሪ ነው፡፡ እና ሁለቱ አብረው ሳይጓዙ አይቀርብ ተብሎ ይታመናል፡፡

ጅደይ በቱኒዝያ በ1957 ዓ.ም. ተወለደ፡፡ ወደ ሞንትሬይል፣ ካናዳ በ1983 ዓ.ም. ገብቶ በ1987 ዓ.ም. የካናዳ ዜግነት አገኘ፡፡ በ1991 ጅደይ ካናዳን ለቆ ወደ አፍጋኒስታን ተጓዘ፣ በዚያም የሽብርተኝነት ስልጠና እና የውጊያ ልምድ አግኝቷል፡፡ ከአፍጋን ሰሜናዊ ትብብር (አፍጋን ኖርዘርን አላያንስ) ጋር የተዋጋ ሲሆን፣ ለጅሀድ ለመሰዋት ያለውህ ሀሳብ የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ በዚህ ወቅት በ1993 ዓ.ም. በአል-ቃዒዳ ቤት ውስጥ በተገኘ የመስዋዕትነት ቪዲዮ ታይቷል፡፡

ጅደይ በ1993 ዓ.ም. ወደ ሞንትሪያል አካባቢ ተመለሰ፡፡ ጅሀድን ለመቀላለቅ ከሌሎች አክራሪዎች ጋር ከተመካከረ በኋለ ካናዳን ለቅቆ ወጥቷል፡፡ ባለስልጣናት ይህ ግለሰብ የሽብር ጥቃት ለፈመፀም ወይም ለማቀደ ወደ ካናዳ ወይም ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሶ ይገባል የሚል ፍርሀት አላቸው፡፡

Skip to content