አብድ አል-ራህማን አል-ማግሪሊ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 7 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ መሀመድ አባታይ ወይም ይበልጥ አብድ አል-ራህማን አል-ማግሪሊ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $7 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል ማግሪቢ በኢራን የሚገኘው የአል-ቃዒዳ (ኤኪው) መሪ ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ የአል-ቃዒዳ የሚዲያ ክንፍ፣ አል-ሳሃብ፣ ዳይሬክተር ሆኖ ቆይቷል፤ እንዲሁም የአል-ቃዒዳ መሪ አይማን አልዛዋሂሪ የጋብቻ ዘመድ እና ከፍተኛ አማካሪ ነው፡

የተገኙ ሰነዶች እንደሚያሳዩት አል-ማግሪቢ ለበርካታ አመታት የአል-ቃዒዳ እየፈነጠቀ የመጣ ኮከብ ነበር፡፡ አልማግሪቢ ከ2004 ጀምሮ የአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን በአል-ቃዒዳ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡ አለም አቀፉ የፀረ ሽብር ጫና ለበርካታ አመታት ከፈጠረበት ውጥረት ምክንያት ወደ ኢራን ተዘዋወረ፤ በዚያም ሆኖ በአለም ዙሪያ የአል-ቃዒዳን እንቅስቃሴዎቸ መምራቱን ቀጥሏል፡፡ የአል-ቃዒዳ የውጭ ኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ሀላፊ እንደመሆኑ መጠን አልማግሪቢ ከአል-ቃዒዳ ተባባሪዎች ጋር በትብብር ይሰራል፡፡

በጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አልማግሪቢ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአልማግሪቢ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልማግሪቢ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content