ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በ2010 ስለተፈፀመው የኒጀር ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
በመስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ቶንጎ ቶንጎ በተባለው የኒጀር መንደር አካባቢ ከአይሲስ – ግሬተር ሰሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) ጋር ግንኙነት የነበራቸው ታጣቂዎች ሽብርተኝነትን በመዋጋት ላይ ለነበሩ የናይጄሪያ ሀይሎች ስልጠና፣ ምክር እና እገዛ ለመስጠት ተመድቦ በነበረው የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ሀይል ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ምክንያት አራት የዩናይትድ ስቴትስ እና አራት የናይጄሪያ ወታደሮች ሞተዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ሁለት ተጨማሪ አሜሪካውያን እና ስምንት ናይጄሪያውን ቆስለዋል፡፡ በጥር 04 ቀን 2010 ዓ.ም. የአይሲስ-ጂኤስ መሪ አድናን አቡ ዋሊድ አል-ሳህራዊ ለጥቃቱ ሀላፊነት ወስዷል፡፡

