ስለ

በተደጋጋሚ የሚነሱ
ጥያቄዎች


ሰስለ ወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ፕሮግራም አንዳንድ መነሻ መረጃዎች ልትሰጡ ትችላላችሁን?

ወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በ1976 ዓ.ም. በተደነገገው ሕግ፣ ፐብሊክ ሎው 98-533 (በ22 U.S.C. § 2708 ሕግ ሆኖ በወጣው) መሠረት የተቋቋመ የወሮታ ፕሮግራም ነው፤ የሚተዳደረውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማቲክ ሰኪዩሪቲ ቢሮ ነው፡፡

የወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ተልዕኮ የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚችል መረጃ ማመንጨት ነው፡፡

በ1976 ዓ.ም. በወጣው ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የወሮታ ለፍትሕ ዋናው ተልዕኮ ከዚህ የሚከተሉትን ለማሳካት መረጃ ለሚሰጥ ወሮታ ማቅረብ ነበር፡-

  • በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ወይም ንብረቶች ላይ ዓለም ዓቀፍ የሽብር ጥቃት የሚያቅድ፣ የሚፈጽም፣ የሚያግዝ ወይም ሙከራ የሚያደርግን ማናቸውም ሰው በቁጥጥር ስር ለማዋል እና በወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ለማስባል፤
  • ከመነሻውም እንዲህ ያሉትን ድርጊቶች ማስረቀረት፤
  • ቁልፍ የሽብር መሪ ለመለየት ወይም ያለበትን ለማግኘት፤
  • ለሽብር ድርጊት የሚውል ገንዘብ እንዲሰናከል ማድረግ

በ2017 ዓ.ም. ኮንግረስ የወሮታ ለፍትሕን ሥልጣን በማሻሻል ከዚህ የሚከተሉትን ለማሳካት የሚያግዙ መረጃዎች እንዲካተቱ አድርጓል፡-

  • ለሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ድጋፍ በማድረግ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሰዎችን የፋይናንስ እንቅስቃሴ ዘዴዎች ማሰናከል፤
  • በውጭ አገር መንግሥት ምሪት ወይም ቁጥጥር ስር በመሆን ስለ ኮምፒውተር ማጭበርበር ወይም ያለአግባብ ስለመጠቀም የተደነገገው ሕግ እንዲጣስ የሚያግዝ ወይም የሚያበረታታን ማንኛውንም ሰው ለመለየት ወይም ለማግኘት፤

የወሮታ መጠን ከ$1 ሚሊዮን በታች እስከ $25 ሚሊዮን ሊሆን ይችላል፡፡

ወሮታ ለፍትሕ ቀደም ሲል የተሰጠ የወሮታ ሃሳብ ያልነበረ ቢሆንም እንኳን ወሮታ ሊከፍል ይችላል፡፡


ወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ምን ያህል ውጤታማ ነው?

ወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የረዱ መረጃዎች ለሰጡ ከ125 በላይ ግለሰቦች ከ$250 ሚሊዮን በላይ ወሮታ ከፍሏል፡፡ እነዚህ ጥረቶች በቁጥር ለመግለጽ የሚያዳግት ንጹሃንን ሕይወት ታድገዋል፡፡


ወሮታዎችን የምታስተዋውቁት እንዴት ነው?

ከወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ዌብሳይት በተጨማሪ፣ መረጃ ሊሰጡ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ለመገናኘት እንድንችል የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ ፖስተሮችን፣ የክብሪት መያዣዎችን፣ ክፍያ የሚፈጸምባቸውን የሬዲዮ እና የጋዜጣ፣ የኢንተርኔት እንዲሁም ማናቸውም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ዘዴዎች እንጠቀማለን፡፡

ስለ ወሮታ ክፍያዎች የምትለቋቸው መረጃዎች እንዴት ያሉ ናቸው?

ምሥጢራዊነት የወሮታ ለፍትሕ (አርኤፍጄ) ፕሮግራም ቁልፍ አካል ነው፡፡ እኛ ወሮታ ለምንከፍልባቸው ጉዳዮች የቀረቡልንን መረጃዎች ወይም የወሮታ ክፍያ የሚያገኙ ግለሰቦችን ስሞች ለሕዝብ ይፋ አናደርግም፤ እንዲያውም ወሮታ መከፈሉንም በይፋ አናሳውቅም፡፡ በአንዳንድ ከፍተኛ ጉዳዮች ወሮታ መከፈሉን ልናሳውቅ የምንችል ቢሆንም እንኳን የተሰጠንን መረጃም ሆነ መረጃውን የሰጠንን ሰው ማንነት አንገልጽም፡፡


ስለ አንዳንድ የወሮታ ለፍትሕ ስኬቶች ወይም ስለ ተፈጸሙ የወሮታ ክፍያዎች አንዳንድ ዝርዝር መረጃዎች ልትሰጡን ትችላላችሁ?

በየካቲት 1987 ዓ.ም. ከዓለም የንግድ ማዕከል የቦምብ ጥቃት ፈጻሚዎች መካከል ራምዚ ዮሱፍ የተባለው ሰው፣ ወሮታ ለፍትሕ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በተሰጠ መረጃ በፓኪስታን በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ ወሮታ ለፍትሕ በፊሊፒንስ በአራት የተለያዩ የወሮታ ክፍያ ዝግጅቶች በርካታ ክፍያዎችን ፈጽሟል፡፡ በግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም. በሕዝባዊ የወሮታ ክፍያ ሥነ ሥርዓት ወሮታ ለፍትሕ በድምሩ $10 ሚሊዮን ክፍሏል፡፡ ፕሮግራሙ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በፊሊፒንስ ይህ ከፍተኛው ክፍያ ነበር፡፡

በቤንጋዚ ሊቢያ የዩናይትድ ስቴትስን አምባሳደር ጨምሮ አራት አሜሪካዊያንን የገደለውን በአሜሪካ ጊዜያዊ ሚሲዮን ፋሲሊቲ እና አኔክስ ላይ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ጠንሳሽ አሕመድ አቡ ኻታላህ እንዲያዝ እና በወንጀል ድርጊቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲተላለፍበት ያስቻለውን መረጃ ለሰጠው ግለሰብ ወሮታ ለፍትሕ እስከ $3 ሚሊዮን ከፍሏል፡፡


ጉዳዩን ግልጽ የማታደርጉ ከሆነ በእውነትም ወሮታ እንደምትከፍሉ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

እንደተገለጸው ሁሉ፣ ወሮታ ለፍትሕ ከፍተኛ ለሆኑ ጉዳዮች ስለከፈላቸው የወሮታ ክፍያዎች ውስን ማስታወቂያዎች ያደርጋል፡፡

እንዲሁም ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለኮንግረስ ምሥጢራዊ ሪፖርት እናቀርባለን፡፡


የወሮታ ተከፋይ ለመሆን ብቁ የሚያደርግ ምንድን ነው? የምትፈልጉት እንዴት ያለ መረጃ ነው?

ከዚህ የሚከተሉትን ለማሳካት የሚያስችሉ መረጃዎች የሚሰጡ መረጃዎች የወሮታ ክፍያ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡-

  • በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ወይም ንብረቶች ላይ በማንኛውም የዓለም ክፍል ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኝነትን ለማስቀረት ወይም ጠቃሚ በሆነ መልኩ መፍትሔ ለማግኘት፤
  • በውጭ አገር የሽብር ድርጅት ውስጥ ቁልፍ መሪዎችን እና መገኛቸውን ለመለየት፤
  • የሰሜን ኮሪያን አገዛዝ ለመደገፍ በአንዳንድ አንቅስቃሴዎች ላይ ያሉ ግለሰቦችን ወይም ተቋማትን የፋይናንስ ዘዴዎች ለማሰናከል፤
  • በውጭ አገር መንግሥት ምሪት ወይም ቁጥጥር ስር በመሆን ስለ ኮምፒውተር ማጭበርበር ወይም ያለአግባብ ስለመጠቀም የተደነገገው ሕግ እንዲጣስ የሚያግዝ ወይም የሚያበረታታን ማንኛውንም ሰው ለመለየት ወይም ለማግኘት፤

የመንግሥት ባለሥልጣናት ካላቸው ይፋዊ ሥራ ውጪ መረጃ ካልሰጡ በቀር በጠቅላላው የወሮታ ክፍያ ለማግኘት ይችላሉ፡፡


አንድ የመረጃ ምንጭ ስለ ሽብርተኛ መረጃ ለመስጠት ለሕይወቱ/ቷ ስጋት ከሆነበት/ባት እና ሕይወቱ/ቷን ስጋት ውስጥ ከወደቀስ? ወሮታ ለፍትሕ ጥበቃ ሊሰጥ ይችላል?

ምሥጢራዊነት ለወሮታ ለፍተሕ የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡ ወሮታ ለፍትሕ መረጃ የሚሰጡትን የመረጃ ምንጮች እና የወሮታ ክፍያ የሚያገኙትን ሰዎች ማንነት በጥብቅ ምሥጢር ይይዛል፡፡ ከዚህም ሌላ እያንዳንዱን ጉዳይ በማየት ለመረጃ ምንጮች እና/ወይም ለቤተሰቡ/ቧ የመኖሪያ ቦታ ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡

ግለሰቦች ክፍያ የሚፈጸምላቸው እንዴት ነው?

ወሮታ ለፍተሕ ክፍያ የሚፈጽመው ጥንቃቄ በተሞላበት ሂደት ነው፡-

  • የዩናይትድ ስቴትስ መርማሪ ኤጀንሲ (እንደ መከላከያ ሚኒስቴር ወይም ኤፍቢአይ) ወይም በውጭ አገር የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለአንድ የወሮታ ክፍያ ብቁ የሆነውን ሰው መጠቆም አለበት፡፡ መረጃ ሰጥተናል የሚሉ ሰዎች ለወሮታ ክፍያ ራሳቸውን ማጨት አይችሉም፡፡
  • በሕግ ረገድ ለክፍያ በቁ የመሆን ጉዳይ ከታየ በኋላ፣ ከልዩ ልዩ ኤጀንሲ የተውጣጣ ኮሚቴ ጥቆማውን በሰጠው ኤጀንሲ የቀረበውን መረጃ በጥንቃቄ ይፈትሻል፡፡ የተሰጠው ጥቆማ ምን ያህል ዋጋ ያለው መሆኑ ከተፈተሸ በኋላ፣ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳቡን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያቀርባል፡፡
  • ሆኖም ግን በኮሚቴው የተሰጠው የውሳኔ ሃሳብ አስገዳጅ አይደለም፡፡ ማንኛውም የወሮታ ክፍያ እንዲከፈል ውሳኔ የመስጠት ሙሉ ስልጣን ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ናቸው፤ በሕጉ በተቀመጠውም አኳኋንም የወሮታውን ክፍያ መጠን ሊቀይሩ ይችላሉ፡፡
  • በፌደራል የወንጀል ፍትሕ ሥልጣን ስር በሚወድቅ ጉዳይ የሚከፈል የወሮታ ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት በክፍያው ጉዳይ ላይ ዋና ዓቃቤ ሕጉ እና የሚንስትሩ ስምምነት አስፈላጊ ነው፡፡
  • ለወሮታ ክፍያ እጩ ሆኖ መቅረብ ክፍያው እንዲፈጸም ስለመፈቀዱ ዋስትና አይሰጥም፡፡ በሚኒስትሩ የሚሰጥ የክፍያ ውሳኔ የመጨረሻ እና በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለም፡፡

የወሮታ ክፍያ መጠኖች የሚወሰኑት እንዴት ነው?

የወሮታ የክፍያ መጠኖች ብዛት በበርካታ ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው፤ ከእነርሱም መካከል፡- የተሰጠው መረጃ ዋጋ፤ በተገኘው መረጃ መሠረት ለመቀነስ የተቻለው ስጋት ደረጃ፤ ይህ ስጋት በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ወይም ንብረት ላይ የሚያደርሰው አደጋ ወይም ጉዳት ጥልቀት፤ የመረጃው ምንጭ እና የእርሱ/ሷ ቤተሰብ የተጋረጠባቸው ስጋት፤ የመረጃ ምንጩ የተባባሪነት መጠን፡፡ ለምሥክርነት የሚከፈል ክፍያ አይኖርም፡፡

ለአንድ የመረጃ ምንጭ የሚከፈለው የክፍያ መጠን እስከተገለጸው የወሮታ የገንዘብ መጠን ድረስ የትኛውም ሊሆን ይችላል፡፡


ወሮታ ለፍተትሕ ከያዘው ዝርዝር የሰረዘው ሰው አለ? ከሆነ ማን እና ለምን?

አዎ፣ በዓመታቱ ሂደት ወሮታ ለፍትሕ ልዩ ልዩ ተጠርጣሪዎችን ከዝርዝሩ ሰርዟል፤ ከእነርሱም መካከል የአል-ቃዒዳ መሪ ኡሳማ ቢን ላዲን እና የአይሲስ መሪ አቡ በከር አል-ባግዳዲ ይገኙባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች ከወሮታ ለፍትሕ ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ሊሰረዙ ይችላሉ፤ ከምክንያቶቹም፣ የተጠርጣሪዎች በሕግ አስከባሪዎች ወይም በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል፤ መሞታቸው እርግጥ ሲሆን ወይም በሌላ ይፋዊ የመረጃ ምንጭ ስጋት መሆናቸው መቅረቱ ሲገለጽ ይካተታሉ፡፡


ወሮታ ከፋዮች መሆናችሁ ተፈላጊዎቹን ለማስገደል የሚፈልጉትን አያበረታታም?

ተፈላጊዎቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልጉ እና ሌሎች ከመንግሥት ውጪ የሆኑ ግለሰቦች ሽብርተኞችን ወይም ሌሎች ከማሳደድ እንዲቆጠቡ አበክረን እናሳስባለን፤ ይልቁን ወሮታ ለፍትህ አግባብነት ያላቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲህ ያሉትን ሰዎች አግኝተው ቁጥጥር ስር እንዲያውሉ የሚያስችሏቸውን መረጃ ለሚሰጡ ወሮታ ይከፍላል፡፡


መረጃ ለመስጠት ከፈለግሁ፣ ማንን ማግኘት እችላለሁ?

መረጃ ያላቸው ግለሰቦች መረጃውን በስልክ ቁጥር (202) 702-7843 በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አማካኝነት በዋትስአፕ፣ ቴሌግራም ወይም ሲግናል መላክ አለባቸው፡፡

በሌላ በኩል መረጃ ያላቸው ግለሰቦች መረጃቸውን በቅርብ ለሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም በቅርብ ለሚገኘው የኤፍቢአይ መሥሪያ ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡


በአቅርቦቴ ወይም በጽሑፌ ላይ ከእናንተ ድረ-ገጽ ያገኘሁትን ማቴሪያል (ምስል) ለመጠቀም እፈልጋለሁ፡፡

ኮፒራይት ካልተመለከተ በቀር፣ በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ የሚገኘው መረጃ ሕዝባዊ ሲሆን፣ በወሮታ ለፍትሕ ሳይፈቀድ ሊባዛ፣ ሊታተም ወይም በሌላ መልኩ ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም፡፡ ወሮታ ለፍትህ የመረጃው ምንጭ መሆኑ እንዲገለጽ እና በተመሳሳይ መልኩ ለማንኛውም ፎቶ ወይም ጽሑፍ እንደ አግባብነቱ ለባለፎቶው ወይም ለጸሐፊው ወይም ለወሮታ ለፍትሕ ዕውቅና እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

ኮፒራይቱ በፎቶ፣ ገራፊክ ወይም ማናቸውም ሌላ ማቴሪያል ላይ የተገለጸ እንደሆነ፣ እነዚህን ማቴሪያሎች ኮፒ ለማድረግ ከዋናው ምንጭ ፈቃድ መገኘት አለበት፡፡ በተጨማሪም፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በ18 U.S.C. 713 በአንዳንድ ሁኔታዎች የዩናይትድ ስቴትስን ታላቅ ማኅተም መጠቀም የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል፤ ስለሆነም በማናቸውም አውድ ታላቁም ማኅተም ከመጠቀም በፊት ከምክር ቤቱ ጋር እንድትመካከሩበት ሃሳብ እናቀርባለን፡፡


RewardsForJustice.net የተባለው ድርአምባ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ድርአምባ መሆኑን የማውቀው እንዴት ነው?

ወሮታ ለፍትሕ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶፕሎማቲክ ጥበቃ አገልግሎት (ዲኤስኤስ) የሚተዳደር ሲሆን፤ በዲኤስኤስ ስር በይፋዊ ድርአምባው ላይ ስለወሮታ ለፍትሕ የሚገልጽ ክፍል አለው፡- Visit External Link፡፡ ይህም ገጽ ሰዎች መረጃዎችን እንዲሰጡበት በቀጥታ ከዚህ ከወሮታ ለፍትሕ የፋዊ ሳይት ጋር ተገናኝቷል፡፡



Skip to content